የኤርትራ ልዑክ ለጥምቀት በዓል ጎንደር ገባ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራ ልዑክ የጥምቀት በዓልን ለመታደም ጎንደር ከተማ ገባ፡፡
ልዑኩ ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ማስተዋል ስዩም እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
ሉዑኩ የተመራው በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርእሶም ነው።
በጎንደር ዛሬ የከተራ በዓል ነገ ደግሞ የጥምቀት በዓል በድምቀት ይከበራል።
ለበዓሉ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የውጭ ሀገራት ጎንደር ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
ዛሬ ማለዳ ላይም ቁጥራቸው ከፍ ያለ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች በበዓሉ ላይ ለመታደም ጎንደር ገብተዋል።
በሶዶ ለማ