በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገ ክትትል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተያዘ፡፡
እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፃ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረው ዶላር የተያዘው ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ላምበረት ተብሎ በሚጠራው መናኸሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
ከህዝብ በተገኘ ጥቆማ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በቅንጅት ባደረጉት ክትትልም ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ሊጓዙ የተዘጋጁ ሁለት ተጠርጣሪዎች በያዙት ሻንጣ ላይ በተደረገ ፍተሻ 110 ሺህ ዶላር ሊገኝ ችሏል ነው የተባለው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

37,035
People Reached
1,562
Engagements
Boost Post
589
23 Comments
51 Shares
Like
Comment
Share