Fana: At a Speed of Life!

ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዘሮችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአለም ምግብና እርሻ ድርጅት በትግራይ ክልል የአርሶ አደር ቤተሰቦች ወደ ግብርና ስራ እንዲመለሱ የሚያስችል አስቸኳይ ፕሮግራም ይፋ አደረገ።

በኢትዮጵያ የፋኦ ተወካይ ፋጡማ ሰዒድ ድርጅታቸው አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የግብርና ምርት ማምረት እንዲጀምሩ ማስቻል ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል።

እንዲሁም ሊመጡ የሚችሉ ችግሮችን መቋቋም የሚችሉበትን አቅም መፍጠር ሌላኛው ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር እንደሆነ መናገራቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአሁን ወቅት ጥራጥሬዎችን ፣ የጤፍ ፣ የስንዴ ፣ የቲማቲም ዘሮችን  የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተመሳሳይ በክልሉ ፍየሎች ፣ በጎች እና ከብቶች በድንበር ተሻጋሪ የእስሳት በሽታዎች እንዳይጠቁ  ክትባት እየሰጠ እንደሆነም ገልጿል።

የእህል ዘሮች ድጋፉ 50 ሺህ አባዎራችን ለማዳረስ ያለመ ሲሆን በተጨማሪ የ100 ሺህ አባዎራዎች የቁም እንስሳትን ለመከተብ እና ህክምና ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.