Fana: At a Speed of Life!

ህገወጥ የጦር መሳሪያ በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተይዟል።

የወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡፋይሳ ቄልቱ ÷የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ የፖሊስ አባላት ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ መነሻውን ጂንካ አድርጎ ከአርባምንጭ አቅጣጫመድረሻውን መሐል ሀገር አድርጎ ሲንቀሳቀስ በመደበኛ ስራ ላይ የነበሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ለቁጥጥር ሲያስቆሙ አሽከርካሪው በመደናገጡና በተሽከርካሪው ላይም አጠራጣሪ ምልክት በማየታቸው ጠንከር ያለ ፍተሻ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ፈታሾችም በተሽከርካሪው ውስጥ ከተለመደው ውጭ የታሰሩ ብሎኖች በመመልከታቸው ለምርመራ ሲጠይቁ ለቤት ፍጆታ15 ኪሎ ቡና ነው በሚል ቢያስተባብሉም በተደረገው ፍተሻ 42 ኪሎግራም የታሸገ ቡና በፌስታል ኮረሪማ ለማዘናጊያ መገኘቱንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም የተሽከርካሪው ውስጠኛው ክፍል ጎን ላይ ያለው ተጨማሪ ብሎን ሲፈታ አስር ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ መገኘቱንና የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ለማጠናከር የሌላ ተሽከርካሪ ሊብሬ በተጠርጣሪዎቹ እጅ ተይዟል ብለዋል።

ዋና ኢንስፔክተሩ አያይዘውም ሕብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን የሀገርን ሰላም እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በመለሰ ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.