ብሔራዊ የአካባቢ መብቶች ፎረም ተመሰረተ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የአካባቢ መብቶች ፎረም መመስረት የኢትዮጵያን የአካባቢ ጥበቃ እና ልማት ለማሳደግ ብሎም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ውጤታማ እንዲሆን ያግዛል ተብሏል።
የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ከዋቸሞ ዩንቨርሲቲ እና ሌሎች ተባባሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ፎረሙን በሃድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ መመስረታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ እስካሁን በኢትዮጵያ የአካባቢ መብቶችን የሚጠብቅና በዘርፉ የሚሰሩ ሌሎች ተቋማትን የሚያስተሳር አሰራር ባለመኖሩ አካባቢን በሚፈለገው ልክ ለመጠበቅና ለማልማት አልተቻለም ብለዋል።
በመድረኩ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ከ45 የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከሲቪክ ማህበራት ጋር በአካባቢ ጥበቃና ልማት ላይ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!