Fana: At a Speed of Life!

የቤልቱ እና የሚኖ የፀሐይ ሐይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ቁምቢ ወረዳ ሚኖ ከተማ የተገነባው የሚኖ የፀሐይ ሐይል ማመንጫ ፕሮጀክትና በባሌ ዞን ለገ ሂዳ ወረዳ የተገነባው የቤልቱ የፀሓይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

ፕሮጀክቶቹ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ነው የተመረቁት።

የቤልቱ የጸሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በ7ሚሊየን ብር የተገነባ ሲሆን፥ 750 ኪሎ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል፡፡

የሚኖ የጸሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 225 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ሐይል የሚያመነጭ ሲሆን፥ በአካባቢው ያሉ የትምህርት እና የጤና ተቋማትን ጨምሮ ከ9 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል መባሉን የዘገበው ኢቢሲ ነው።

የኤሌክትሪክ ሃይል ላላገኙት የሚኖ ከተማ ነዋሪዎች ፕሮጀክቱ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እንደሚያመጣላቸው ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.