Fana: At a Speed of Life!

በ800 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባው የደገሀቡር ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በ800 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባው የደገሀቡር ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

በመሰረት ድንጋይ ማሰቀመጥ ስነስርዓቱ ምክትል ርዕሰ መሰተዳድሩ፣ የክልሉ የስራ ሀላፊዎችና የደገህቡር ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በስነስርዓቱ የክልሉ ዉሃና ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብራህማን አህመድ ሀሰን እንዳሉት ፕሮጀክቱ፥ በ1 ዓመት ከ8 ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የገለጹ ሲሆን፥ ከተማዋ በቀን ከ9ሺህ ሜትር ክዩብ ውሃ ያሰፈልጋታል ብለዋል።

ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑት የዞኑና አካባቢ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በበኩላቸው፥ ለዉጡን ተከትሎ የክልሉን ህዝብ በየዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እንደተሰሩ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.