Fana: At a Speed of Life!

በ31 ሚሊዮን መነሻ ካፒታል የተቋቋመው ላንሴት ስፔሻላይዝድ የሕክምና ማዕከል ተመረቀ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያውያን ሐኪሞች የጋራ ባለሃብትነት የተቋቋመው ላንሴት ስፔሻላይዝድ  ሕክምና ማዕከል ተመርቋል።

የጤና ማዕከሉ በ24 ስፔሻሊስት እና ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች በ31 ሚሊዮን መነሻ ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ሕክምና ላይ ያላቸውን እምነት ለማሳደግ ይሠራል ተብሏል።

የጤና ማዕከሉ በሀገሪቱ ሆስፒታሎች የሚታየውን የአቅም ውስንነት በመሸፈን በተበጣጠሰ መልኩ የሚሰጠውን የግል ሕክምና በአንድ ጠንካራ ማዕከል ለመስጠት እንደሚያግዝ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዶ/ር ሔኖክ ሰይፈ ተናግረዋል።

ጤና ማዕከሉ ወደ ውጪ የሚደረገውን የሕክምና ጉዞ ለማስቀረት እና አዲስ አበባን የሕክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እንደሚሠራም ነው ዶ/ር ሔኖክ የገለጹት።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ፣ ማዕከሉ በከተማዋ ያሉ የጤና ተቋማትን ሸክም የሚያቃልል መሆኑን ጠቅሰው፣ ከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ዶ/ር ዮሐንስ ጤና ማዕከሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የታካሚዎችን አቅም ባገነዘበ መልኩ አገልግሎቱን ሊሰጥ እንደሚገባውም ተናግረዋል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ  ማዕከሉ ሥራ ከጀመረ አምስት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን ከ3 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሕሙማን አገልግሎት እንደሰጠ እና 350 የተሳኩ የቀዶ ጥገና ሕክምና መስጠት ችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.