የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 12 የኩላሊት ዕጥበት ማሽኖች ድጋፍ ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 12 የኩላሊት ዕጥበት ማሽኖች በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ተደረገለት።
የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ግርማ አበበ በዩኒቨርሲቲ ሆስቲታሉ ያለውን አገልግሎት በተወሰነ መንገድ ለማሳደግ ድጋፉን ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አሸናፊ ታዘበው በዩኒቨርስቲው ከአሁን ቀደም ሁለት የኩላሊት ዕጥበት መስጫ ማሽኖች አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
የማሽኖቹ ድጋፍ መደረግም በቀን የሚስተናገዱትን ከስምንት እስከ አስር የሚደርሱ ታካሚዎችን ቀጥር ወደ 24 ያሳድገዋል ብለዋል።
ማሽኖቹ 13 ሚሊየን ብር ወጭ የተደረገባቸው ሲሆን ከ12ቱ ማሽኖቹ 3ቱ ለደብረታቦር ሆስፒታል የሚሰጡ ናቸው ተብሏል።
በክብረወሰን ኑሩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን