Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የተፈጠረው ሰላም በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ አስችሏል – አቶ ሙስጠፌ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ሰላምና መረጋጋት ግብርናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ አስችሏል ሲሉ የክልሉ ርዕስ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ።

የሶማሌ ክልል ለረዥም ዓመታት በግጭት ድባብ ውስጥ መቆየቱን አስታውሰው አቶ ሙስጠፌ ÷ ከለውጡ በኋላ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ተፈጥሮ ሕዝቡ በሁሉም መስክ የልማት ተጠቃሚ ሆኗል ብለዋል

በተለይም በግብርና፣ ኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በመሳብ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን ጠቅሰው÷ ከለውጡ በኋላ የግብርና ምርት ልማት በእጥፍ ማደጉን ተናግረዋል።

በክልሉ ሁለት ዞኖች ብቻ ከ8 ቢሊየን ብር ያላነሱ ሰፋፊ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች እየተካሄዱ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በዝናብም ሆነ በበጋ መስኖ ልማት ሰፋፊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ጠቁመው÷የስንዴና የሩዝ ልማት በስፋት እየተመረተ ይገኛል ብለዋል።

የምግብ ሰብሎችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባሻገር ለውጭ ገበያ በማቅረብ ሀገራዊ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።

በክልሉ የቱሪዝም ዘርፉ እንቅሰቃሴ ደካማ እንደነበር ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ አሁን ላይ ዘርፉን ለማጎልበት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ለዘርፉ መነቃቃት የላቀ አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.