Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች የምግብና አልባሳት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በጸጥታ ችግር ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብና አልባሳት ድጋፍ ተደረገ።

በሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም ከተጠሪ ተቋማትና የተለያዩ አካላት ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ተከናውኗል።

ከተሰበሰበው 137 ሺህ ኪሎ ግራም የህፃናት አልሚ ምግብ፣ የምግብ ዘይትንና አልባሳት ውስጥ ለመተከል ዞን የተመደበውን 37 ሺህ ኪሎ ግራም ድጋፍ በጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑካን ቡድን በአካል ተገኝቶ አስረክቧል።

የዞኑ የተቀናጀ ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስትና የዞኑ አመራርና ሥራ ኃላፊዎች ድጋፉን ተረክበዋል።

መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ሊያ፥ በመተከል፣ በትግራይና በአጣዬ ለተፈናቀሉ ወገኖች 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ መሰብሰቡን አስታውሰዋል።

የዞኑ የተቀናጀ ግብረ ኃይል ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰት ግጭት ንብረት የወደመባቸውንና ተፈናቃዮችን ለመርዳት የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሰላም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ አጎራባች ክልሎችና የፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በጠቅላላ 137 ሺህ ኪሎ ግራም ከሚሆነው ድጋፍ ውስጥ 66 ሺህ ኪሎ ግራም ለመቐለ፣ 35 ሺህ ኪሎ ግራም ለአጣዬ መመደቡ እንደተገለጸ ይታወሳል።

በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በባህልና ቱሪዝም እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር በኩል የተሰበሰበውን ደጋፍ በየአካባቢው ለዜጎች በማድረሱ ሂደት ሚኒስትሮቹ እንደሚያስተባብሩ ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.