Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችና የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ቂምቢቢት ወረዳ ከ159 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡

በወረዳው የተገነቡ ፕሮጀክቶችን በኦሮሚያ የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳባ ደበሌ የተመራው ልዑክ ቡድን መርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡

የሸኖ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሀ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ባለ አምስት ወለል የመንግስት ሴክተር ፅህፈት ቤቶች ህንፃ ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ምስራቅ ሸዋ ዞን በመተሀራ ከተማ በ26 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች የተመረቁ ሲሆን፥ ፕሮጀክቶቹን የኦሮሚያ ገበያ ልማት ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ አቡኔ ቱሳ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

ትምህርት ቤት፣ የገበያ ማዕከል፣ ሼዶች እና የጎርፍ መውረጃ ቦይ በከተማው ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በተጨማሪም በአርሲ ዞን ዲክሲስ ወረዳ የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክትን በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ የተመራው ልዑክ ቡድን መርቆ ከፍቷል፡፡

በፕሮጀክቱ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.