Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ ከ3 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሰረተ ልማቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ በ3 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሰረተ ልማቶች ተመረቁ፡፡
ፕሮጀክቶቹ ከከተማ አስተዳደሩ፣ ከዓለም ባንክ፣ ከጥረት ኮርፖሬት፣ ከክልሉ መንግስትና ከፌደራል መንግስት በተገኘ ገንዘብ የተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የተመረቁት መሰረተ ልማቶች የኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ ቤተሰብ መምሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ግንባታ፣ የኮብልስቶን ስራዎች፣ የትራፊክ መብራት፣ የሮቢት ገበያ ማሻሻያ ግንባታ ስራ፣ የክላስተር ሼድ ግንባታ፣ የመናፈሻ ተቋም መንገድ፣ የቄራ አገልግሎት ማሻሻያና ሌሎችም ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡
እነዚህ ፕሮጀክቶች በጠቅላላ 3 ቢሊየን 935 ሚሊየን 662 ሺህ 861ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ተነግሯል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የአማራ ክልል ብልፅግና ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ፣ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ መሃመድ፣ የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀልና ሌሎች የክልልና የከተማዋ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ፎቶ፡-ደሴ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን
በሰብለ አክሊሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.