Fana: At a Speed of Life!

የቡኢ የኤሌክትሪክ ሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የቡኢ የኤሌክትሪክ ሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተመረቀ፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል።
የሀይል ማከፋፈያው ቡኢ ከተማን ጨምሮ 22 ከተሞችንና የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተደራሽ እንደሚያደርግ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ የሀይል ማከፋፈያው ግንባታ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 7 ሚልየን 154 ሺህ 276 ዶላር ብድርና ከመንግስት በተገኘ 39 ሚሊየን 320 ሺህ 425 ብር በጀት የተገነባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የሃይል ማከፋፈያው ለተጀመሩም ሆነ አዲስ ለሚጀመሩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርና የክልሉን ልማት እንደሚያፋጥን ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በበኩላቸው ቀደም ሲል በከተማዋ የልማት ስራ ለመስራት እቅድ ነድፈው በሀይል እጦት የሸሹት የአካባቢው ነዋሪዎችም ተመልሰው መጥተው የመስራት እድላቸውን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
የቡኢ ከተማ ከንቲባ አቶ ዘማች እንዳለ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ እንደመሆኗ የሀይል ማከፋፈያ ጣቢያው መገንባቱ አዳዲስ ባለሃብቶችን ወደ ከተማዋ ገብተው እንዲሰሩ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።
ተጨማሪ ፎቶ ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን
በታምሩ ከፈለኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
.
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.