Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከኢትዮጵያዉያን ማህበረሰብ አደረጃጀት መሪዎች ጋር ዉይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አደረጃጀት መሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

በወቅቱም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በፀረ -ሰላም ሀይሎች በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በመንግስት በኩል እየተደረገ ስላለው ጥረት እና በውጭ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሊደረግ ስለሚችል ድጋፍ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያውያኑ በበኩላቸው ወቅቱ በአንድነት መቆምን የሚጠይቅ እንደሆነ አንስተው፥ ለዜጎች አስፈላጊውን እርዳታ ለማሰባሰብ እና በግላቸው አቅማቸው በፈቀደ ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.