Fana: At a Speed of Life!

በ2ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የተገነባው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት 9 ወራት ሲሰራ የነበረው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል።

ፕሮጀክቱ መስቀል አደባባይ ያለውን ስፍራ የቀድሞ ይዘቱን ሳይቀይር ሁለት የግንባታ አካል ወደ ውስጥ በመግባት የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም አደባባዩንና ጎዳናዎችን የማስዋብ ሥራ ነው የተሰራው፡፡
ከዚህ ቀደም ሲሰጥ የነበረውን ሃይማኖታዊ ፣ህዝባዊ እና ሌሎች ማህበራዊ ዝግጅቶች በተለይ በከተማዋ ብዙኃንን ታሳቢ ያደረጉ ኩነቶችን በተሻለ እና ምቹ በሆነ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ የተገነባ ነው፡፡
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በአካባቢው የሚስተዋለውን የተሸከርካሪ ማቆሚያ ስፍራ ጥበትን ከመቅረፍ አንጻር እስከ 1ሺህ 400 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎችን የሚያስቆሙ ባለሁለት የመሬት ውስጥ የግንባታ መሰረቶች ስማርት ፓርኪንግ አለው፡፡
በተጨማሪም 35 ሱቆች፣ 140 መፀዳጃና 20 መታጠቢያ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች የቢሮ መገልገያ ክፍሎች፣ 6 ዘመናዊ ሊፍቶች፣ ለ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ የደህንነት ካሜራዎች፣ ዘመናዊ ዲጂታል ስክሪኖች እና የእሳት መከላከያ ጭምር አለው፡፡
ከዚያም ባለፈ የቴሌኮም፤ባንክ ፤ሱቆች 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ አሉት፡፡
ሱቆቹ የኢትዮጵያን ባህል እና ቅርሶች የሚያሳዩ እና ለጎብኚዎች እንዲሸጡ በሚያመች ሁኔታ ተገንብተዋል፡፡
ቦታው ታሪካዊ ቅርስነቱን ጠብቆ ለደመራ እንዲሆን ተዘጋጅቷል፣ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሆኖ ነው የተገነባው፡፡
እሳት አደጋ አንዱ ጋር ቢከሰት እዚያው እያለ የትም ሳይዛመት መጥፋት የሚችልበት ሙቀት መከላከል በሚችል መልኩ /natural and coolant/ ቴክኖሎጂን ይዞ ነው የተገነባው፡፡
በመስቀል አደባባይ እና አካባቢው ነጻ የWiFI ኢንተርኔት አገልግሎትም እንዲሰጥ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በሰኔ 2012 ዓ.ም የተጀመረው ይህ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ለግንባታ ስራው 2 ቢሊዮን 589 ሚሊዮን 800 ብር በጀት መጠናቀቅ ችሏል ነው የተባለው፡፡
ላለፉት 9 ወራት 24 ሰዓታት ቀን እና ለሊት ሲሰራ ነበረ ሲሆን ለ10 ሺህ ወጣቶች ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.