በዳንሻ ከተማ የአሸባሪው ሕወሃትን ግፍ የሚያወግዝ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ ከተማ የአሸባሪውን ሕወሃት ግፍ የሚያወግዝና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዷል።
በአሸባሪው ሕወሃት የሥልጣን ዘመን የደረሰውን ግፍ የሚያወግዙና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወሙ ሰልፎችም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራና የተለያዩ ከተሞች ሲደረጉ መቆዬታቸው ይታወሳል።
በሑመራ ከተማ የተጀመረው ሰልፍም ዛሬ በዳንሻ ከተማ የቀጠለ ሲሆን፥ ነዋሪዎቹ የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ግፍ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰልፍ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!