Fana: At a Speed of Life!

መስቀል አደባባይ ከሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ የሚገናኙበት፣ብዙ ታሪክ ያሳለፈ የሁላችንም አደባባይ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) መስቀል አደባባይ ከሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ የሚገናኙበት፣ብዙ ታሪክ ያሳለፈ የሁላችንም አደባባይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል።

መስቀል አደባባይ ከሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ የሚገናኙበት፣ብዙ ታሪክ ያሳለፈ የሁላችንም አደባባይ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) መስቀል አደባባይ ከሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ የሚገናኙበት፣ብዙ ታሪክ ያሳለፈ የሁላችንም አደባባይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህንን የተናገሩት በ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የተገነባውን የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ዛሬ በመረቁበት ወቀት ነው፡፡

ዛሬ የመረቅነው አደባባይ የመሰብሰቢያችን ለሁላችንም የሚመጥን አደባባይ በመሆኑም እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

የመስቀል አደባባይ ብዙ ያየ ብዙ ያሳለፈ የማንነታችን ክፋይ የመሰብሰቢያችን ሲሳይ ነውያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ÷ ልማት እንደማጥፋት፤ ማደስ እንደ ማፍረስ ቀላል አይደለም ብለዋል፡፡

የብዙ ሀገር መሪዎችን ተቀብሎ አስተናግዷል፣ በህልፈተ ህይወት የተሰናበቱ ታላላቅ መሪዎችን ሸኝቷል።

በመስቀል ደመራ በአል ደምቋል፣ ታላላቅ የህዝብ በአላትን አስተናግዷል፣ የድጋፍና የተቃውሞ ሰልፎችን በትዝብት አይቷል፣ በየማለዳው የአካል ብቃት ሯጮችንና ስፖርተኞችን አደግድጎ ተቀብሏል ነው ያሉት።

ስሙ ተለዋውጣል፣ የአብዮት አደባባይ ሆኖ የመሪዎችን ቁጣና የህዝብን እምባ በአርምሞ ታዝቧል፣ የምርጫ 97 እና የሰኔ 16ን የህዝብ የገነፈለ ስሜት በሰፊ ሆዱ ተሸክሞ አሳልፏል ነው ያሉት።

የሀገሪቱ ብቸኛ ታላቅ አደባባይ እንደመሆኑ የመጣውን ታላቅ ሁነት ሁሉ ለብቻው እንደአመጣጡ ተቀብሎ ሸኝቷል ሲሉ ገልጸዋል።

በአዘቦት ቀን ደግሞ ወናውን ተሰጥቷል፣ አላፊ አግዳሚውን በትዝብት ተመልክቷል።

የትናንት ጠባሳ የነገ አበሳ እንዳይሆን መትጋትይጠበቅብናል፣ተሰናስለን ከተጋን ያማረች ኢትዮጵያን መፍጠር  እንችላለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ።

ሁላችሁም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ኢትዮጵያን ወደታላቅነት እንድናደርሳት ጥሪ ላደርግላችሁ እፈልጋለሁም ነው ያሉት ።

የአፍሪካ ስልጣኔ የሁላችንም ሲሆን÷ጠንክረን ከሰራን የአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ክንድ ይሆናልም ብለዋል።

በዚህም የሚታደስም አዲስ የሚፈጠር ስልጣኔን መፍጠር  እንችላለን  ኢትዮጵያን የአፍሪካ ክንድ እናደርጋታለን ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ እንደ ቅኔ ናት፤ እኛ እንደንገጣሚ ነን፤ ልጆቻችን ናቸው የሚያነቡን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልፅግና የሚወለደው በልጆቿ ትብብር እና አንድነት ነው፤ ሳይነቀነቅ ገለባን የሚለይ ወንፊት የለምና የአሁኑ  መነቅነቃችን ገለባን ከመለየት አይገታንም፤  ስንሠራ የሚረዱ፣ የሚረዱ እና የሚርዱ አሉ ብለዋል።

ከአንድ ሣምንት በኋላ በቁጥር ስድስተኛ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ምርጫ ይካሄዳል፤ እየመረጥን አሻራችንን እናኑር  ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.