Fana: At a Speed of Life!

በ300 ሚሊየን ብር ለሚገነባው የጎንደር ከተማ የቄራ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ300 ሚሊየን ብር ለሚገነባው የጎንደር ከተማ የቄራ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ እና የከተማው የአገልግሎትና አቅርቦት አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮሎኔል ዘለቀ አለባቸውን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎችና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ ግንባታው በተባለው ጊዜ እንዲጠናቅ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት ሊሰራ ይገባል፡፡

በፍጥነት ወደ ስራ በመግባትም ከጎንደር ባለፈ የቄራ አገልግሎት በመስጠት እና የስጋ አቅርቦት ላይ በመስራት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ በበኩላቸው፥ ጎንደር ከተማ በተቀናጀ የከተሞች ልማት የተለያዩ የመሰረተልማት ስራዎችን እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የከተማው የአገልግሎትና አቅርቦት አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮለኔል ዘለቀ አለባቸው፥ የቄራ ግንባታው በሁለት አመት እንደሚጠናቀቅ ጠቅሰው፥ በቀን ከ200 በላይ የእርድ እንስሳት ለገበያ እንደሚቀርቡ አስረድተዋል፡፡

ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት ሲጀምርም ከ300 በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል፡፡

በሰላም አስመላሽ

ፎቶ – አሚኮ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.