የአዌቱ ወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ተመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በጅማ ከተማ የተገነባው የአዌቱ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት መርቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን ያስመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
በሙክታር ጠሃ፣ አላዛር ታደለ እና ተመስገን አለባቸው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!