Fana: At a Speed of Life!

በአሶሳ ከተማ የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ እና ማበልፀጊያ ፋብሪካ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንሻንጉል ገሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ እና ማበልፀጊያ ፋብሪካ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ እህት ኩባንያ በሆነው ናሽናል ኮል ኩባንያ የሚገነባው ፋብሪካው 2 ቢሊየን ብር ወጪ ይደረግበታል ተብሏል።

የመሰረት ድንጋዩን የቤንሻንጉል ገሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትር ኢንጅነር ታከለ ዑማ፣ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የቦርድ አባል አቶ አብነት ገ/መስቀል አስቀምጠዋል።

ፋብሪካው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን እስከ አንድ ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል የማምረት አቅም ይኖረዋል መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.