የጎንደር ከተማ ም/ቤት የህገ-ወጥ ተኩስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ መመሪያ አፀደቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የጎንደር ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የህገ-ወጥ ተኩስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ መመሪያ አጽድቋል፡፡
የጎንደር ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 8ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን፥ ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል የህገ-ወጥ ተኩስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ መመሪያ መርምሮ ማፅደቅ ፣ የምክር ቤቱን የ4ኛ ዙር 8ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ ዋና ዋናዎቹ አጀንዳዎች ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ በትኩረት ከተወያበት አጀንዳ መካከል አንዱ የሆነውን የህገ-ወጥ ተኩስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ መመሪያ መርምሮ ማፅደቅ ሲሆን፥ ረቂቅ ደንቡ ምክር ቤቱ በህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ በንባብ ቀርቦለት አድምጧል፡፡
መመሪያው በንባብ ቀርቦ ከተደመጠ በኃላ የምክር ቤቱ አባላትም አስተያየቶችን መስጠታቸውን ከጎንደር ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከተማዋ የቱሪስት መዳረሻና የኢኮኖሚ ኮሪደር በመሆንዋ ምንም ጥይት የማይተኮስባት ከተማ ለማድረግ መመሪያው አጋዥ መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በመመሪያው ላይ ስፊ ውይይት ካደረጉ በኃላ መመሪያውን በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡
የፀደቀው የህገ-ወጥ ተኩስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በምክር ቤቱ የወጣው ረቂቅ መመሪያ ሶስት ክፍሎች እንዳሉትም ለመረዳት ተችሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!