Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የመኸር ግብርና ልማትን ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን ገለጹ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመኸር ግብርና ልማትን ጨምሮ በክረምቱ ወራት የሚከናወኑ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ፡፡

በክልሉ ያለውን ሰላም በማጽናት በሕዝቡ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው አቶ ኡሞድ የገለጹት፡፡

እስካሁን በርካታ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸው÷ በቀጣዩ ክረምትም የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ነባርና አዲስ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲከናወን ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በመጪው የመኸር ወቅት ከ164 ሺህ ሄክታር በላይ በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በመጪው ክረምት ለሚካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከ14 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.