Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተደርጓል – የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ)ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መራጩ ህዝብ የደህንነት ስጋት ሳይሰማው ድምፁን እንዲሰጥ በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ጠንካራ ጥበቃ ለማድረግ ሙሉ ዝግጅት ማደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ አስታውቀዋል፡፡

በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ሁለትና ከዚያ በላይ የፖሊስ አባላት መመደባቸውን ያስታወቁት ኮማንደር ፋሲካ፥ እንደ የሁኔታው አስገዳጅነት ፍተሻ እየተደረገ ኃይል የሚጨመርበት አሠራር መዘርጋቱንም ገልጸዋል፡፡

ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ከበቂ በላይ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት ኮማንደሩ፥ ለትግበራው ከክልል ማዕከል ጀምሮ እስከ ከተማ፣ ወረዳ እና ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በየደረጃው ኮማንድ ፖስት መዋቀሩን አመልክተዋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከየፌዴራል መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የተዋቀረ መሆኑን መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.