Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መድረጉን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለጿል፡፡

በዞኑ በ13 የምርጫ ክልሎች በ1 ሺ 128 የምርጫ ጣቢያዎች ነው ምርጫ የሚከናወነው፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ተወካይ ሃላፊ ኮማንደር ብዙነህ አጎናፍር እንደገለጹት÷ የፖሊስ አባላት ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅና ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩል ለማገልገል ዝግጁ ናቸው፡፡

በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ ሃይል መሰማራቱን የገለጹት ኮማንደር ብዙነህ÷ በምርጫው ዕለት ችግር ቢፈጠር አፋጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የኦፕሬሽንና ምርመራ ቡድን መዋቀሩንም አንስተዋል፡፡

በምርጫው ዕለት ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የመንግስትን ተሽከርካሪ እንዳይጠቀም ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መደረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡

ምርጫው ሲጠናቀቅም የምርጫ ኮሮጆዎችን በማግስቱ ጠዋት በማጀብ ወደ ማዕከል የማምጣት ስራ ለመስራት በፖሊስ በኩል ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከ664 ሺህ በላይ መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን÷ 6 ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ለውድድር ቀርበዋል፡፡

በአላዩ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.