Fana: At a Speed of Life!

በአንዳንድ አካባቢዎች የድምጽ አሰጣጥ ተጠናቆ ድምጽ ቆጠራ ተጀምሯል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻግኒ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ድምጽ መስጠት ተጠናቆ ቆጠራ ተጀምሯል፡፡

ደብረ ብርሃን ከተማን ጨምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የተካሄደው ምርጫ በሰላም ተጠናቆ ማምሻውን ቆጠራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን የቃኘ ሲሆን÷ በዚህ ሰዓት የምርጫ ታዛቢዎች ባሉበት ቆጠራ እየተካሄደ መሆኑን ተመልክቷል።

ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቱም ነገ ጠዋት በየምርጫ ጣቢያዎቹ ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ በሃዋሳ ፣ በወልዲያ እና ድሬዳዋ ከጠዋቱ 12 ሰዓት የተጀመረው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ተጠናቆ ድምጽ ቆጠራ ተጀምሯል፡፡

በተያያዘም ሰሜን ወሎ ዞን ባሉ ዘጠኝ የምርጫ ክልሎች ድምፅ የመስጠት ሂደት ተጠናቆ ቆጠራ ተጀመረ፡፡

የዞኑ ምርጫ ቦርድ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አይንየ ተፈራ እንደገለፁት ምርጫ በተካሄደባቸው 1 ሺህ 43 የምርጫ ጣቢያ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር ሳይከሰት ምርጫው በሰላም ተጠናቆ ወደ ቆጠራ ተገብቷል፡፡

በይስማው አደራው፣ ስንታየሁ መሃመድ፣ አላዩ ገረመው፣ ሳምራዊት የስጋት እና በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.