Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ ተአማኒና ሰላማዊ ነበር – የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ ተአማኒና ሰላማዊ ነበር ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ተናገሩ።

ታዛቢ ቡድኑ ከምርጫ ቅስቀሳው አንስቶ እስከ ምርጫው እለት ያለውን ሂደት መከታተሉን የጠቀሱት የታዛቢ ቡድኑ መሪ የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በቀር የቅስቀሳ ሂደቱ በፓርቲዎች ዘንድ ፍትሃዊነቱ የተጠበቀ ነበር ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ያደረገው ጥረትም የሚመሰገን መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በምርጫው እለት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሳዩት ተሳትፎ መልካም ነበር ያሉት የቡድን መሪው ኢትዮጵያ ተአማኒና ሰላማዊ ምርጫ አካሂዳለች ብለዋል።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ እድገት የምታደርገውን ጥረት እንዲያግዝም ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ጥሪ አቅርበዋል።

የታዛቢ ቡድኑ የከተማና የገጠር አካባቢዎችን ጨምሮ 5 ክልሎችን እንደታዘበ መግለጹን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.