Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ታዬ ከጽህፈት ቤቱ ዳይሬክተር ሬና ጌላኒ እና ምክትል ዳይሬክተር ጋዳ ኤልታሂር ጋር መወያየታቸውን በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ካለው ሰብአዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጽህፈት ቤቱ በማስረጃ የተደገፈ ዘገባ ሊኖረው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በክልሉ የሚደረገው እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በአግባቡ መድረሱን ለማረጋገጥ ከመንግስት ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.