ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደት እና ቀጠናዊ ትብብር እንዲጎለብት ትሰራለች – አቶ አሕመድ ሺዴ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማምጣት እና ቀጠናዊ ትብብር እንዲጎለብት ጠንካራ ፍላጎት እንዳላት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ ገለጹ።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ከጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ እና ሱዳን የገንዘብ ሚኒስትሮች ጋር በምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ ላይ መክረዋል።
በምክክሩ ላይ ንግድ፣ የሃይል ዘርፍ እንዲሁም ዲጂታል ኢኮኖሚ የመወያያ አጀንዳ መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በመድረኩ የአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ በታዛቢነት ተሳትፈዋል።
የኢኒሼቲቩ የወቅቱ ሊቀ-መንበር የጂቡቲ ገንዘብ ሚኒስትር አያስ ሙሳ ዳዋሌህ ኢኒሼቲቩ በቀጠናው ቅድሚያ ለተሰጣቸው ዘርፎች የሚሆን 3 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር መሰባሰቡን ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም ኢኒሼቲቩ ቅድሚያ ሰጥቶ ላጸደቃቸው ዋና ዋና ተግባራት 15 ቢሊየን ዶላር ለማሰባሰብ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!