Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የታደሰውን የእናት አርበኛ ወ/ሮ ማሚቴ ምህረቱ ቤት አስረከቡ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የታደሰውን የእናት አርበኛ ወ/ሮ ማሚቴ ምህረቱ ቤት አስረከቡ።

የከተማ አስተዳደሩ ባለሀብቶችን እና በጎፍቃደኛ ግለሰቦችን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን እና ለሀገር የሰሩ ባለውለታዎች ለመደገፍ አየተሰራ ነው።

አስታዋሽ ያጡ አረጋዊያንን መደገፍ ሁሉም ባለሀብቶች እና በጎ ፍቃደኞች ሊሳተፉበት ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት የታደሰው ቤትም የዚህ ትብብር አካል ነው ብለዋል።

ይህን ቤት በፍጥነት አድሰው ላስረከቡት አቶ ሙኒር ሀይረዲን እንዲሁም የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ላደረጉት አቶ አለማየሁ ንጉሴን በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል ።

በዘንድሮው የክረምት ወራትም በከተማዋ ከ2ሺህ በላይ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ተጀምሯል።

የከተማ አስተዳደሩ የሀገር ባለውለታዎቻችን አስታውሶ ቤታቸውን ከማደስ አልፎ እና ለተደረገላቸው የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ መደሰታቸውን የገለፁት እናት አርበኛ ወ/ሮ ማሚቴ ምህረቱ ምስጋና ማቅረባቸውን ከአስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.