Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 28 ጀምሮ ይሰጣል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ከ17 ሺህ በላይ ተማሪዎችም ለፈተና እንደሚቀመጡ ቢሮው አመልክቷል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት ክልል አቀፍ ፈተናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀው በ186 የፈተና ጣቢያዎች 523 ፈታኞች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በፈተናው ላይ 10 ሺህ 319 ወንድ እና 7 ሺህ 639 ሴት ተማሪዎች በድምሩ 17 ሺህ 958 የቀንና የማታ ተማሪዎች እንደሚቀመጡ አስታውቀዋል፡፡
ፈተናው በሚሰጥበት ቀንም ሆነ የፈተናው የጥያቄ ወረቀት የማጓጓዝ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን በየዘርፉ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ፈተናው በሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶችም ከ150 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል እቅድ መያዙን ጠቁመው ለስኬታማነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻውን ሊያበረክት እንደሚገባ አቶ ሙሴ ማሳሰባቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.