Fana: At a Speed of Life!

ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ስደተኞችን መልሶ ለማቋቋም ከመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ስደተኞችን መልሶ ለማቋቋም ከመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ።

የፌዴራል ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢዜአ እንደገለፁት÷ከቅረብ ጊዜ ወዲህ ከሳውዲ አረቢያ ለሚገቡ ስደተኞች ፈጣን መፍትሄ ስለሚያስፈልጋቸው ልዩ እቅድ በማወጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።

አቶ ንጉሱ  በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎች ላይ ለተከሰተው ችግር ፈጣን መፍትሄ ለመስጠት ልዩ እቅድ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

ከስደት ለተመለሱት ዜጎች በፍጥነት የስራ ዕድል ሊመቻች የሚቻልበተን ሁኔታ በመቅረፅ፣ በማቀድ እንዲሁም ሃብት በማፈላለግ እና በሥራ ስምሪት ረገድ የተለያዩ ተግበራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ ተግባር የተቋማትን ትብብርና ድጋፍ የሚጠይቅ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።

ለዚህም ኮሚሽኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራን መሆኑን ነው የተናገሩት።

ከፌዴራል እስከ ክልል ባሉ የመንግስት ተቋማት መዋቅር ተዘርግቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ÷ ከስደት በመመለስ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ከአየር መንገድ ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ተመላሾቹ ወደ አገር ከገቡ በኋላ ለማቋቋም በሰላም ሚኒስቴር የሚመራ ግብረ ሃይል ከተለያዩ ተቋማት መቋቋሙን ተናግረዋል።

በየአካባቢያቸውም ሄደው ባላቸው የትምህርት ደረጃ ልምድ እና የቤተሰብ ሁኔታ ታይቶ የስራ ዕድል እየተፈጠረላቸው መሆኑ ገልፀዋል።

ስደተኞቹ በእስር ቤት ብዙ ስቃይና መከራ የደረሰባቸው መሆኑን ያስታወሱት ወይዘሮ አየለች÷ በስነ ልቦና ባለሙያዎች ድጋፍ እየተደረገላቸው ወደ አካባቢያቸው እንዲሄዱ  እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግ መሆኑን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.