Fana: At a Speed of Life!

በምርጫው ብልጽግና ፓርቲ ካሸነፈ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንደተሳትፏቸው በመንግስት መዋቅር ውስጥ ውክልና እንዲኖራቸው ያደርጋል-ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ተሳትፏቸው ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ውክልና ወይም ተሳትፎ እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
የምርጫ ውጤቱ በተቃራኒ ሆኖ ብልጽግና ፓርቲ የሚሸነፍ ከሆነም የኢትዮጵያን አሸናፊነት ለማረጋገጥ መንግስት ለአሸናፊው የፖለቲካ ፓርቲ ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ እንደሚያስረክብም ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒትሩ ይህን ያሉት የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ምክር ቤት “ኢትዮጵያ አሸንፋለች እና እናመሰግናችኋለን” በሚል ባዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም ላይ ነው፡፡
በምርጫው እለት ዜጎች ኢትዮጵያ አሸናፊ እንድትሆን ወጥተው ድምፅ በመስጠታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያዊያን ከፖለቲካ ይልቅ አገር ትቀድማለች የሚል መርህ አንግበው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ አገራቸውን አሸናፊ አድርገዋልም ነው ያሉት።

በጥበበስላሴ ጀንበሩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.