Fana: At a Speed of Life!

የሳይበር ጥቃት አድራሹ ቡድን ለመረጃ ማስለቀቂያ 70 ሚሊየን ዶላር እንዲከፈለው ጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ኮሎሳል’ በሚል ከሚታወቀው የኮምፒውተር መረጃ ጥቃት ጀርባ ያለ የሳይበር ጥቃት አድራሽ ቡድን ለመረጃ ማስለቀቂያ 70 ሚሊየን ዶላር እንዲከፈለው ጠየቀ።

ዘ_ሬቭል በሚል የሚታውቀዉ የመረጃ መንታፊ ቡድን አሜሪካ ውስጥ ባለ ‘ካስያ’ የተባለ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋም ላይ የመጀመሪያዉን ጥቃት ማድረሱን ቢቢሲ ጠቁሟል።

ከዚያ   የሳይበር ጥቃት በኋላ ግን  የመርጃ መንታፊ ቡድኑ ከአንድ ሚሊየን በላይ የኮምፒውተር ሥርዓቶችን ማጥቃቱን  አስታውቋል።

የመረጃ መንታፊ ቡድኑ የጠየቀው 70 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ በቢት ኮይን ሲከፈለው÷ የግል መረጃቸውን ያገደባቸው ሰዎች መረጃቸውን እንዲያገኙ እንደሚፈቅድ ገልጿል።

ቡድኑ የኮምፒውተር መረጃ ጥቃት ያደረሰው በምን ያህል ሰዎች እንደሆነ በግልጽ እንደማይታወቅ የተገለጸ ቢሆንም ስዊድን ውስጥ የሚገኙ 500 መደብሮች እና 11 የኒው ዚላንድ ትምህርት ቤቶች የመረጃ ምዝበራ ከተደረገባቸው መካከል ይገኙበታል ተብሏል።

ሆኖም ሀንትረስ የተባለው የበይነ መረብ ደህንነት ተቋም ወደ 200 የሚሆኑ ድርጅቶች ጥቃት እንደደረሰባቸው ገምቷል።

የመጀመሪያው ጥቃት ሰለባ የሆነው ካስያ የተባለው ተቋም ወደ 40 የሚጠጉ ደንበኞቹ ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው አረጋግጧል።

ካስያ ሶፍትዌር የሚያቀርብላቸውና ሌሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ  አገልግሎት የሚሰጡ ተቋሞች በስሩ  ስለሚገኙ ጥቃቱ መጠነ ሰፊ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

የካስያ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬድ ቮካላ ለአሶሺየትድ ፕሬስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት÷ የበይነ-መረብ ጥቃት የደረሰባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ወደ አንድ  ሺህ ሊጠጉ ይችላሉ ብለዋል።

ይህም ቤተ መጻሕፍት እና የጥርስ  ህክምና ማዕከላትን ጨምሮ ነው ብለዋል።

ጥቃቱን ለማስቆም አንድ የኔዘርላንድ ተቋም ጥረት ቢያደርግም የበይነ መረብ ጥቃት አድራሹ ቡድኑ ሬቭልን ማስቆም ሳይችሉ ቀርተዋል።

ፕሮፌሰር ሲራን ማርቲን የተባሉ የበይነ መረብ ደህንነት ጥበቃ ባለሙያ “ይህ ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ ጥቃት ያልተጠበቀና ውስብስብ ነው” ማለታችዉን ቢቢሲን ጠቅሶ ኢመደኤ  ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.