Fana: At a Speed of Life!

”ደጀን ወደ ሆነው ሕዝባችን ስንገባ የተደረገልን አቀባበል ሰራዊቱን ያስደመመ ነው‘ – ኮሎኔል ሻምበል በየነ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)”ደጀን ወደ ሆነው ሕዝባችን ስንገባ የተደረገልን አቀባበል ሰራዊቱን ያስደመመ ነው‘ ሲሉ  ኮሎኔል ሻምበል በየነ ባለከዘራው የ23ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ገለጹ።

ጁንታው ገደልን ማረክን እያለ ማሳሳት የኖረበት ባህሪው መሆኑንም ነው የገለጹት ።

ኮሎኔል ሻምበል በየነ በአማራ ክልል ዋግኽምራ አስተዳደር ዞን አበርገሌ ወረዳ ስንደርስ በህዝቡ የተደረገልን አቀባበል ደማቅ እና ሰራዊቱ የህዝብ ሰራዊት መሆኑን በተጨባጭ ያሳየ ነው።

እኔ በግሌ የህዝቡን አቀባበል የምጠብቀው ቢሆንም  በሰራዊቱ ዘንድ በዚህ ደረጃ አቀባበል ይደረጋል ብሎ አልጠበቀም ነበር።

በያለፍንባቸው አካባቢዎች ሕዝቡ ለሰራዊቱ ያለውን ፍቅር የገለጸበት መንገድ ከፍ ያለ የሞራል ስንቅ የሚሆን ነው ብለዋል።

ህዝቡ ለሰራዊቱ የሚበላም የሚጠጣም በማቅረብ ለሰራዊቱ ያለውን ድጋፍ በተግባር አሳይቷል።

በተለያየ ደረጃ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል አቀባበሉ የተለየ ነው። ይህ በጣም ተአምር ነው ብለዋል።

በእዚህ ምክንያት መከላከያ ያቀረበልንን ምግብ መጠቀም አልቻልንም ሲሉ አመልክተዋል።

ጁንታው የውሸት ፕሮፖጋንዳን እንደ አንድ የውጊያ ስልት በማድረግ ይጠቀማል በዚህም ያልማረከውን ማረኩ፤ ያልገደለውን ገደልኩ ማለቱ አዲስ አይደለም።

”ባለከዘራው ኮሎኔልን ከበነዋል፣ ማርከነዋል፣ ገድለነዋል” የዚሁ ባህሪው መገለጫ ነው ብለዋል።

እኔን ማረኩ ገደልኩ ሲል የነበረው እኔ ከሌላው አመራር የተለየሁ ሆኜ ሳይሆን በሕዝቡና በሰራዊቱ ያለኝን ተቀባይነት ግምት ውስጥ በማስገባት ላሰለፋቸው ታጣቂዎች የተዳከመ የሞራል አቅም ለመገንባት ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.