Fana: At a Speed of Life!

የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት “ኑ ኢትዮጵያን እናልብሳት” የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በየካ ሚሊኒየም ፓርክ አከናውነዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገዥና ተቃዋሚ የሚለው የፖለቲካ ትርክት እየተቀየረ በአንድ በኩል በሀሳብ ፉክክር በሌላ በኩል ደግሞ በሀገራዊና ከተማዊ ጉዳዮች የመተባበር ባህል መጎልበቱን አውስተዋል፡፡
መርሃ ግብሩ አረንጓዴ አሻራን ከማሳረፍ በተጨማሪ ለዴሞክራሲ ግንባታም አስተዋፅኦ እንዳለው የገለፁት ኃላፊው ÷ በቀጣይም የትኛውም ፓርቲ ያሸንፍ በሀገራዊ ጉዳዮች በጋራ እንደምንቆም ያሳየንበት ነው ብለዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶከተር ራሄል ባቴ በበኩላቸው÷መሪዎች ራዕይ ወደ ህዝብ ወርዶ ፍሬያማ የሚሆነው የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በሀገራዊ ጉዳዮች በጋራ ሲቆሙ ነው ብለዋል።
ያሸነፈም የተሸነፈም እኩል ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ልማት ላይ በጋራ እንሰራለን ያሉት ዶክተር ራሄል÷ ቀጣዩን ትውልድ ለመገንባት ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም በማየት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተሳተፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን አመስግነዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ተክሌ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች በክረምት የተከልናቸውን ችግኞች በበጋው ወቅትም በጋራ መንከባከብ እንደሚገባ ጥሪ ማቅረባቸው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.