ኢትዮጵያ ምርጫውን በስኬት ስላጠናቀቀች ቻይና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ምርጫውን በስኬት ስላጠናቀቀች ቻይና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡
ቻይና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይዋ ሊያን ዣኦ በኩል ነው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቷን ያስተላለፈችው፡፡
በመልዕክቱም፥ ኢትዮጵያ ያካሄደችውን ምርጫ ስኬታማ በሆነ መልኩ ማጠናቀቋን በመግለጽ በቀጣይ አገራቱ በትብብር ለሁለቱም አገራት ህዝቦች ተጠቃሚነት አብረው እንደሚሰሩ ገልጻለች፡፡
ኢትዮጵያ የቻይና ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ለቻይና አፍሪካ ትብብርም ኢትዮጵያ ቁልፍ ናት ሲሉም በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!