የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች ችግኝ ተከሉ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ማሳረፍ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡
አመራሮች እና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሽዋ ዞን በሊበን ጭቋላ ወረዳ ዶሎሎ ጅላ ቀበሌ ከታ ሀሜቲ ተራራ ላይ ነው አረንጓዴ አሻራቸውን ያሳረፉት፡፡
በመርሃ ግብሩ ከ30 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማጠናከር እና ከአሁን በፊት የተተከሉትን በመንከባከብ እና በሌሎች ማህበረሰብ አቀፍ በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ፣ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል፣የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አምበሳው እንየው እና ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ