Fana: At a Speed of Life!

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እርዳታ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እርዳታ አደረገ፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለጌርጌስዩን አእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል  እና  በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በእሳት አደጋ ምክንያት ሀብት ንብረታቸውን  አጥተው   በጊዜያዊ መጠልያ ውስጥ  ለሚገኙ ተጎጂዎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ የተደረገው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስት ርዶክተር ሂሩት ካሳው  እና የባህል ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ  ወይዘሮ ብዙነሸ መሰረት በተገኙበት ነው፡፡

በዚሁ ወቅት ዶክተር ሂሩት ካሳው  እንደተናገሩት ÷ ይሄን መሰል የድጋፍ ስራዎች  የአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት የሚቀጥል ነው ብለዋል።

አያይዘውም እንደነዚህ ያሉ የበጎ አድራጎት ስራዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ሊበረታቱ ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.