Fana: At a Speed of Life!

ከኦሮሚያ ክልልና ከአማራ ክልል  የተውጣጡ ወጣቶች በጣርማ በር ወረዳ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  ከኦሮሚያ ክልልና ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተውጣጡ  ወጣቶች በጣርማበር ወረዳ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

መርሃ ግብሩ የሁለቱን ህዝቦች ትስስር ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ÷  ወጣቶች እርስ በእርስ ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር ለሀገር እድገትና ለአብሮነት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

አያይዘውም እንዲህ አይነት መድረኮች ለዚህ መንገድ ከፋች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው የዛሬው ችግኝ መርሃ ግብር የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ትስስር መሰረቱ የጠነከረ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በመሃሀ ግብሩ ከ4ሺህ በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ከ500 በላይ ተሳታፊዎችም ተገኝተዋል፡፡

በአይናለም ስለሺ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.