Fana: At a Speed of Life!

ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ተቋማት በትብብር እንዲሰሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬት ተቋማት በትብብር እንዲሰሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።

“የአንድ ዓመት ጉዞ- ዲጂታል ኢትዮጵያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ” በሚል “የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ 2025” ፀድቆ ወደ ስራ ከገባበት ጀምሮ የተሰሩ ስራዎችና በቀጣይ ሊሰሩ በሚገባቸው ስራዎች ዙሪያ የሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ መክረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ ባለፈው አንድ አመት ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታ መፍጠር፣ የዲጂታል ስትራቴጂ 2025 ምንነትን ማሳወቅና ተቋማት በእቅዳቸው ውስጥ እንዲያካትቱት የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።


የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን በማድረግ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተቋማት በትብብር እንዲሰሩ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

በዝግጅቱ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ የኢኖቬሽን ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ በርካታ ስራዎች ስለመሰራታቸው ተብራርቷል።

በዝግጅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት፣ ከስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲቲዩትና ሌሎችም የሚመለከታቸው ተቋማት ኃላፊዎች የዘርፉ ስራዎችን የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራሙ ስር ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ስለተሰሩ ስራዎች ገለፃ መደረጋቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.