Fana: At a Speed of Life!

የህዝብን ፍላጎት ያማከለ የፖለቲካና የልማት ስኬት ተመዝግቧል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2013 በጀት አመት የህዝብን ፍላጎት ያማከለ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካና የልማት ስኬት መመዝገቡን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ፡፡

የኦሮሚያ ክልል የ2013 በጀት አመት  የስራ አፈጻጸምና የተያዘው በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ በአዳማ ገልማ አባ ገዳ መገምገም ጀምሯል፡፡

በተለይ በግብርናው ዘርፍ በቡና፣ በአቩካዶ፣ በሰብልና በመስኖ የስንዴ ልማት ውጤታማ ስኬት መመዝገቡን  ነው አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጠቅሰዋል፡፡

እየተከናወነ ባለው የ2013/14 ምርት ዘመን የመኽር ግብርና ስራ አንድም መሬት ጦም እንዳያድር ታሳቢ ተደርጎ ሊከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በተመሳሳይ የክልሉ ህዝብ አሸባሪውን ህወሓትን ጨምሮ የውስጥና የውጭ ጠላትን በምርጫው በመቅጣት፣ ለህዳሴው ግድብ ድጋፍ በማድረግና በህልውና ዘመቻው እያደረገ ባለው ተሳትፎ  አመርቂ ስኬት መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

በዘንድሮው 3ኛው ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀንበር ከ300 ሚሊየን በላይ ችግኝ በመትከል አዲስ ስኬት  መመዝገቡን  ርዕሰ መስተዳድሩ  ጠቅሰው÷ የችግኝ ተከላው ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ  በበኩላቸው ÷የክልሉ ህዝብ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያሳየው ንቁ ተሳትፎ የሀገር ቀጣይነትና ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“በምርጫው የተመዘገበው ስኬት 2ኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በስኬት በማጠናቀቅ ድርብ ድል አስመዝግበናል” ብለዋል፡፡

በግምገማ መድረኩ በ2013 በጀት አመት የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ለ2014 በጀት አመት  የጋራ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.