Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 5ኛ የምርጫ ጊዜ 6ኛ የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ጁል ናንጋል እንዳሉት ÷በክልሉ ያለውን ሰላም ይበልጥ በማጠናከር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል፡፡
ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመቆም የተከፈተብንን ሀገር የማተራመስ ሴራ መመከትና የህግ ማስከበር ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል ከሁሉም እንደሚጠበቅ አመልክተዋል፡፡
በህወሃት የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረግ ከሁሉም የክልሉ ህዝቦች እንደሚጠበቅም አፈ-ጉባኤው ማስታወቃቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡
ጉባኤው ለሶስት ቀናት በሚኖረው ቆይታ ያለፈውን በጀት ዓመት የክልሉን የልማትና የመልካም አስተዳደር፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች የእቅድ ክንውን ሪፖርት አዳምጦ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የ2014 በጀት ዓመት የክልሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ እና የ2014 በጀት ዓመት የክልሉ ረቂቅ በጀትን መርምሮ ከማጽደቅ በተጨማሪ የተለያዩ አዋጆችና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.