Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ 2 ሺህ 455 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያስተማራቸውን 2 ሺህ 455 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 845ቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት የዛሬዎቹን ጨምሮ 20 ሺህ 36 ምሩቃንን ለሀገር አበርክቷል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልፀው የፒ ኤች ዲ መርሃ ግብር ለማስጀመር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑንምጠቁመዋል።

ሀገር በቀል ዕውቀትን ከቴክኖሎጅ ጋር በማዋሃድ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉትል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኦርጎጌ ተስፋዬ ተማሪዎች እውነትን እና ስነምግባርን በማስቀደም ዕውቀታቸውን እንዲጠቀሙበት መልዕክት አስተላልፋዋል ።

በዛሬው ዕለት ከተመረቁ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የሶማሊያ እና የደቡብ ሱዳን ዜጎች ይገኙበታል።

በክብረወሰን ኑሩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.