Fana: At a Speed of Life!

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ132 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ ታስቦ በተሰራው ዘመናዊ የሃብት ማሰባሰቢያ ሥርዓት አማካኝነት 132 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃይሉ አብረሃ እንደተናገሩት÷ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ለግድቡ ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በቅርቡም ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ድረ ገጽ መተግበሪያ በኢትዮጵያዊያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በልጽጎ ይፋ ሆኗል።

መተግበሪያው በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሚኖሩበት ቦታ ሆነው እንደ አቅማቸው የፈለጉትን የገንዘብ መጠን ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላቸው ነው።

ይሄው በገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሄራዊ ባንክና ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዕውቅና የተሰጠው http://xn--www-snp.mygerd.com/ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ድረ-ገጽ፤ በቀላልና አስተማማኝ መንገድ ከፈቃደኛ ለጋሾች ለግድቡ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ድረገጹ በኢትዮጵያ መረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በኩል እውቅና ያለውና ድጋፍ ሰጭውን የማያጠራጥር ዘመናዊ ሥርዓት ሲሆን÷በዚሁ የድረ ገጽ ዘመናዊ የሀብት ማሰባሰብ መንገድ እስከአሁን ከ1ሺህ27 ለጋሾች 132 ሺህ ዶላር መሰብሰብ ተችሏል።

ህዝቡም በቀጣይ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሃላፊው ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.