Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ጓድ አባላት ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግሰት ጎን እንደሚቆሙ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሰላም ጓድ አባላት ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግሰት ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ከተመራው የሰላም ጓድ አባላት ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

የሰላም ጓድ አባላት በኢትዮጵያ እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች በመደሰታቸው ምስጋና ለማቅረብ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግሰትና ህዝብ ጎን መቆማቸውን ለማረጋገጥ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን የቡድኑ አስተባባሪ ፕሮፌሰር ብሩክ ገልጸዋል፡፡

በአሜሪካ ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የቡድኑ አባላት በማሳተፍ በልማት ሥራዎች፣ በተራድኦ ተግባራት እና በሀገር ገጽታ ግንባታ እያበረከቱ ያሉት የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ለአቶ ደመቀ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ቡድኑ እያደረገ ስላለው በጎ ተግባራት እና ከኢትዮጵያ ጎን በመቆማቸው ምስጋና አቅርበው÷ ሥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

በተያያዘም መንግስት የቡድኑን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳለው ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.