Fana: At a Speed of Life!

የማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን ፣ የፕላን ኮሚሽን እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት የወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን፣ የፕላን ኮሚሽን እና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የወር ደመወዛቸውን ድጋፍ ለማድረግ ወሰኑ፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራርና ሰራተኞች ዛሬ ባካሄዱት ውይይት÷ለሀገር ህልውና ለሚደረገው ዘመቻ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ያብባል አዲስ ÷ ኢትዮጵያ ወደ ቀውስ እንድታመራ እየጣረ ያለውን አሸባሪ ቡድን በመዋጋት የሀገራችንን የአይደፈሬነት ታሪክ ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ ሁለንተናዊ ርብርብ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች የበኩላቸውን ድጋፍ በማድረግ በአንድነት የሀገራችንን ህልውና ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ወቅቱ ሀገሪቷን ለውጭ ወራሪ አጋልጦ ለመስጠት የሚደረግ ታሪክ የማይረሳው የአሸባሪ ድርጊት እንደሆነ ማውገዛቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ መቼም ለጠላት ተንበርክካ እንደማታውቅ ሁሉ አንድነታችንን ጠብቀን ለህልውናችን በአንድነት በመቆም ከወር ደመወዝ መለገስ ባሻገር በሚፈለገው ሁሉ ድጋፍ ለማድረግና ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን ለመቆም መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ተጠሪ ተቋማት ከሆኑት የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡

 
በዛሬው እለት በተካሄደው ሥነ ሥርዐት ላይ ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋን ጨምሮ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.