Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በየደረሰበት ስፍራ በህፃናት እና ሴቶች ላይ የጅምላ ግድያ ፈጽሟል-አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በየደረሰበት ስፍራ ህፃናት፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ላይ የጅምላ ግድያ መፈጸሙን የአፋር ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስታወቁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሀገር ሽማግሌዎችና ማህበረሰብ መሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የህወሓት ሽብር ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስና ህዝቦቿን ለማተራመስ የጀመረው ጥረት እንደማይሳካለት ተናግረዋል፡፡
የአፋር ህዝብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አላስደፍርም በማለት መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ሁላችንም ባለንበት ለሀገራችን የቻልነው ሁሉ በማድረግ ግዴታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል።
አሸባሪው ህወሓት በእብሪት ተወጥሮ በክልሉ የፈጸመውን ወረራ ለመቀልበስ እየተወሰደ ያለው የአጸፋዊ ምላሽ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.