Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ጀርመን የሚኒስትሮች ኮሚሽን የባለሙያች የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ ጀርመን የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን የባለሙያች የምክክር መድረክ ተጠናቋል።

በውይይት መድረኩ ሁለቱ ወገኖች በሰኔ ወር 2011 ዓ.ም በበርሊን በተፈራረሙት የጋራ ኮሚሽን ስምምነት መሰረት እና የሀገራቱን የጋራ ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አዳዲስ የትብብር መስኮችን መጀመር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

መድረኩ ሁለቱ ሀገራት በውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ጉዳዮች፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ልማት፣ በሰዎች ዝውውር፣ በሃይል እና አየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ መድረኮች የሚያደርጓቸውን ትብብሮች ማጠናከር በሚያስችሉ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በመምከር እና የተዘጋጀውን ቃለ ጉባኤ በመፈራረም ተጠናቋል።

በምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ በኩል በአውሮፓ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ የተመራ ልዑክ መሳተፉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.