Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ኢንስፔክተር ሰለሞን ባረጋ የኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጠው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ፖሊስ ስፖርት ክለብ አባል የሆነዉ አትሌት ኢንስፔክተር ሰለሞን ባረጋ የኮማንደርነት ማዕረግን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ ተሰጥቶታል፡፡

በቶክዮ ኦሎምፒክ የተሳተፈዉ ልዑካን ቡድን በደቡብ ክልል ሀዋሳ ከተማ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን÷ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ ለአትሌቶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል::

ስፖርት በባህሪዉ ከአዝናኝነት ባሻገር የማህበረሰብን ትስስር ለማጠናከርና በህዝብ ዘንድ መተሳሰብና መቀራረብን ለማዳበር ወሳኝ መሆናቸዉን ኮሚሽነሩ አንስተዋል፡፡

የደቡብ ፖሊስ ስፖርት ክለብ በተለያዩ ስፖርታዊ ወድድሮች ብቁ አትሌቶችን በማብቃት የሀገርን ስም በአለም አደባባይ ከፍ አድርጎ በማስጠራት ሚናዉን እየጫወተ መሆኑን ተናግረዋል::

በእግር ኳሱ ዘርፍ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አጥቂዉ ጌታነህ ከበደን ያነሱት ኮሚሽነር ነብዩ÷ በአትሌቲክስ በተለያዩ ርቀቶች የተለያዩ አትሌቶች በአለም አቀፍ የዉድድር መድረኮች ኢትዮጵያን ወክለዉ እንዲወዳደሩ ማድረጋቸዉን ገልጸዋል፡፡

አሁን ደግሞ በ10ሺህ ሜትር ወንዶች ኢንስፔክተር ሰለሞን ባረጋ ፣ በድንቅ ችሎታዉ ኢትዮጵያን አኩርቷል ብለዋል::

በአቀባበል ስነስርኣቱ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳዉን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር ፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና ሌሎችም ተገኝተዋል::

አሁን በአትሌትክስ ዘርፍ የተለያዩ ስኬቶችን ላስገኙ አሰልጣኝና አትሌቶች ሽልማቶች እየተበረከተላቸዉ ይገኛል፡፡

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.